ቦይንግ 787 ድሪምላይነር
ቦይንግ 787 ድሪምላይነር በቦይንግ የተሠራ የረዥም ርቀት፣ ጥንድ ሞተር አውሮፕላን ነው። የአውሮፕላኑ አብዛኛው ክፍሎች ከካርቦን ኮምፖሲት ማቴሪያል በመሠራታቸው፣ አውሮፕላኑ ከቀደምት አውሮፕላኖች የቀለለ ነው።[1] የነዳጅ ፍጆታው ከሌሎች አውሮፕላኖች በ20 ከመቶ የተሻለ ሲሆን ፍጥነቱ ከድምፅ ፍጥነት በ11 ከመቶ ያንሳል።[1] ጃፓን ከዓለም የመጀመሪያው የድሪምላይነር አብራሪ ናት። ኢትዮጵያ ከዓለም ሁለተኛ፣ ከአፍሪካ ደግሞ ብቸኛዋ አብራሪ ናት።[1] የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጠቅላላ አሥር ድሪምላይነሮችን በ1.5 ቢሊዮን ዶላር ገዝቷል።[1] ከተገዙት አሥር አየር-ዠበቦች የመጀመሪያውና በሰሌዳ ቁጥር ET-AOQ የተመዘገበው አየር-ዠበብ ነሐሴ ፲፩ ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ከዋሽንግተን ዲሲ ተነስቶ አዲስ አበባ፣ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ደማቅ አቅባበል ተደርጎለታል።[2]
ማመዛገቢያ
- ^ ሀ ለ ሐ መ ሪፖርተር ጋዜጣ፣ ቅፅ 17 ቁጥር 49/1284፣ ነሐሴ ፲፫ ቀን ፳፻፬ ዓ.ም. የወጣ፣ ገጾች 4፣55
- ^ http://www.flightglobal.com/news/articles/ethiopians-first-787-arrives-at-addis-ababa-375615/
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |