አትሬዩስ
አትሬዩስ በጥንታዊ ግሪክ አፈ ታሪክ ዘንድ የሙከናይ ከተማ-አገር ንጉሥ ነበረ።
ልክ መቼ ይገዛ እንደ ነበር ያልተወሰነ ነው፤ የሙከናይ ሥልጣኔ በግሪክ አገር ምናልባት ከ1600-1100 ዓክልበ. ያህል እንደ ቆየ ይታሥባል። ይህ ከትሮያ ጦርነት በፊት በሆነው ጨለማ ዘመን ነበር።
በትውፊቱ መሠረት አትሬዩስና ወንድሙ ጡወስቴስ ለንጉሥነቱ እጩዎች ነበሩ። በመጀመርያ የከተማ ሕዝብ ጡወስቴስን ይምረጡ ነበር።
ያንጊዜ በተአምር ፀሐይ በቀን ወደ ኋለ ተመልሶ ወደ ምሥራቁ አድማስ እንደ ተጓዘ ታያቸው።
ከዚህ ክሥተት የተነሣ የከተማ ሕዝብ ሀሣባቸውን ቀይረው ንጉሥነቱን ለአትሬዩስ ሰጡት።
በኬጥያውያን መንግሥት መዝገቦች ደግሞ አንድ «አታርሲያ» የተባለው የአሒያውያን (ግሪኮች) ንጉሥ ተገኘ። ይህም «አታርሲያ» የአትሬዩስ ስም በኬጥኛ እንደ ሆነ በአንዳንድ መምህሮች ይታሥባል።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |