አዛኒያ

አዛኒያ በ1728 ዓም ካርታ

አዛኒያ (ግሪክኛ፦ Ἀζανία) በታሪካዊ ምንጮች ውስጥ በምሥራቅ-ደቡባዊ አፍሪካ የተገኘ አገር ነበር።[1]ሮሜ መንግሥት ዘመንና ምናልባት ከዚያም በፊት፣ ከሶማሊያኬንያ ጀምሮ[2] እስከ ታንዛኒያ ድረስ ያለው የሕንድ ውቅያኖስ ዳርቻ አገር ሁሉ «አዛኒያ» ተብሎ ነበር። የባንቱ ፍልሰት እዚያ ከደረሰ በፊት በተለይ የኩሻዊ ቋንቋ ተናጋሪዎች ይገኙበት ነበር።[3]

«የቀይ ባሕር ጉዞ መዝገብ» በ50 ዓም ግድም በግሪክ ተጽፎ ስለ አዛኒያ ይገልጻል። ከአፍሪቃ ቀንድ እስከ ራፕታ ወደብ ድረስ (በአሁን ታንዛኒያ) ይዘርጋል፤ ይህም ራፕታ የአዛኒያ ደቡባዊ ጫፍና መርካቶ ይባላል።[4] የዝሆን ጥርስና የኤሊ ቅርፊት በራፕታ ወደብ በንግድ እንደ ተገኙ ይላል። በዚህም ጽሑፍ ዘንድ የአዛኒያ ባህር ዳር እስከ አሁኑ ሞዛምቢክ ድረስ ለሒምያር (የመን) ንጉሥ ካሪብ ኢል ተገዥ ነበር።

ትልቁ ፕሊኒ እንደ ጻፈ፣ «የአዛኒያ ባሕር» (N.H. 6.34) ከአዱሊስ መርካቶ (በአሁኑ ኤርትራ) ጀምሮ፤ ከዚያም የአፍሪካ ቀንድን ዞሮ ወደ ደቡብ ይገኝ ነበር። ከፕሊኒ በኋላ ክላውዲዎስ ቶለሚ (150 ዓም ግድም) እና ኮስማስ ኢንዲኮፕሌውስቴስ (550 ዓም) ደግሞ ጠቅሰውታል።.ኮስማስ እንዳለ በዘመኑ ለአክሱም መንግሥት ተገዥ ነበር፤ ጥጃ በወርቅ እዚያ ይገዛል ይላል።

በ250 ዓም አካባቢ በተጻፉ ቻይንኛ ሰነዶች አቅራቢያው /ዜሳን/ (澤散) ተባለ።[5]

የባንቱ ፍልሰቶች ከ950 ዓም ያህል ደረሱ።[6] ከዚህ በኋላ የባሕር ዳር አገር በአረቦች «ዘንጅ» ይባል ነበር፤ ይህም ስያሜ አሁን በዛንዚባርና በ«ታንዛኒያ» መጠሪያዎች ይታያል።

ከዚህ በላይ ባለፈው ክፍለ ዘመን አንዳንድ ወገኖች በደቡብ ሱዳንደቡብ አፍሪካሶማሊያ «አዛኒያ» የሚለውን ስም ወድደውት ለራሳቸው በድረውታል።

ደግሞ ይዩ


ተዋቢ መጻሕፍትና የውጭ መያያዦች

  1. ^ Collins & Pisarevsky (2004). "Amalgamating eastern Gondwana: The evolution of the Circum-Indian Orogens". Earth-Science Reviews. 
  2. ^ Richard Pankhurst, An Introduction to the Economic History of Ethiopia, (Lalibela House: 1961), p.21
  3. ^ https://scholar.lib.vt.edu/ejournals/ElAnt/V1N5/hilton.html
  4. ^ George Wynn Brereton Huntingford, The Periplus of the Erythraean Sea, (Hakluyt Society: 1980), p.29
  5. ^ "Weilue: The Peoples of the West. Draft translation by John Hill". Depts.washington.edu (2004-05-23). በ2016-12-27 የተወሰደ.
  6. ^ Fage, John. A History of Africa. Routledge. pp. 25–26. ISBN 1317797272. https://www.google.com/books?id=mXa4AQAAQBAJ በ20 January 2015 የተቃኘ. 
  • Casson, Lionel (1989). The Periplus Maris Erythraei. Lionel Casson. (Translation by H. Frisk, 1927, with updates and improvements and detailed notes). Princeton, Princeton University Press.
  • Chami, F. A. (1999). "The Early Iron Age on Mafia island and its relationship with the mainland." Azania Vol. XXXIV 1999, pp. 1–10.
  • Chami, Felix A. 2002. "The Egypto-Graeco-Romans and Paanchea/Azania: sailing in the Erythraean Sea." From: Red Sea Trade and Travel. The British Museum. Sunday 6 October 2002. Organised by The Society for Arabian Studies.[www.thebritishmuseum.ac.uk/ane/fullpapers.doc]መለጠፊያ:Dead link
  • Collins, Alan S.; Pisarevsky, Sergei A. (2005). "Amalgamating eastern Gondwana: The evolution of the Circum-Indian Orogens". Earth-Science Reviews 71: 229–270. doi:10.1016/j.earscirev.2005.02.004. 
  • Huntingford, G.W.B. (trans. & ed.). Periplus of the Erythraean Sea. Hakluyt Society. London, 1980.
  • Yu Huan, The Weilue in The Peoples of the West, translation by John E. Hill [1]

Preview of references

  1. ^ "Weilue: The Peoples of the West" (2004-05-23). በ2016-12-27 የተወሰደ.