ኡር-ናንሼ
![](http://upload.wikimedia.org/wikipedia/commons/thumb/4/4b/Relief_Ur-Nanshe_Louvre_AO2344.jpg/270px-Relief_Ur-Nanshe_Louvre_AO2344.jpg)
ኡር-ናንሼ ከ2314 እስከ 2284 ዓክልበ. ድረስ ግድም የሱመር ከተማ ላጋሽ መጀመርያ ንጉሥ ነበር። ቀዳሚው ሉጋል-ሻግ-ኤንጉር ንጉሥ ሳይሆን አለቃ ወይም ከንቲባ ነበር፤ ለመሲሊም ተገዥ ነበር። ከመሲሊም ዘመን በኋላ ላጋሽ ነጻ ወጣ። ኡር-ናንሼ የጉኒዱ ልጅ ነበር። ንግሥቱ መንባራ-አብዙ ተባለች። በዘመኑ ግድግዳዎች፣ ቤተ መቅደሶችና መስኖዎች እንደ ተሠሩ ይመዘገባል። ከድልሙን ጋር ንግድ ያካሄድ ነበር። በዚህ ዘመን የላጋሽ ጎረቤቶች ኡማና ኡር ጦርነት በላጋሽ ላይ አደረጉ፤ ኡር-ናንሼ ግን አሸነፋቸውና የኡማ ንጉሥ ፓቢልጋልቱክን ማረከው። የኡር-ናንሼ ልጅ አኩርጋል ተከተለው።
ቀዳሚው ሉጋል-ሻግ-ኤንጉር |
የላጋሽ ገዥ | ተከታይ አኩርጋል |