አንኮር ዋት

አንኮር ዋት፣ ካምቦዲያ

አንኮር ዋት በአንኮር፣ ካምቦዲያ በ1140 ዓም ግድም የተጨረሰ ዝነኛ ሥነ ሕንጻ ነው። በመጀመርያ የሂንዱ ሃይማኖት ጣኦት የቪሽኑ ቤተ መቅደስ ነበረ። ሕንጻው ከ1200 ዓም በፊት ግን የቡዲስም ገዳም ሆነ። ፍርስራሹ እስካሁንም ድረስ በአንኮር ከተማ ሊታይ ይችላል።