ኦሬክ
ኦሬክ (ሱመርኛ፦ /ኡሩኡኑግ/፣ አካድኛ: /ኡሩክ/፣ ግሪክ: Ορχόη /ኦርቆዔ/ ወይም Ωρύγεια /ኦሩገያ/፣ አረብኛ፦ وركاء /ዋርካ/) የሱመር ጥንታዊ ከተማ በኤፍራጥስ ወንዝ ላይ ነበረ። በአለሙ ላይ ከሁሉ ጥንታዊ ትልቅ ከተሞች አንዱ ነው።
ጥንታዊ ሠፈሩ ደግሞ ኩላብ ወይም ኡኑግ-ኩላባ ይባል ነበር። በሱመር ነገሥታት ዝርዝር ዘንድ እንዲሁም በአፈ-ታሪክ «ኤንመርካርና የአራታ ንጉሥ» ዘንድ የመሠረተው ንጉስ ኤንመርካር ነበር። እንዲሁም በመጽሐፈ ቅዱስ ምስክር ዘንድ በሰናዖር የመሠረተው ናምሩድ ነበር (ዘፍጥረት 10፡10)። በኋላ ዘመንም የጊልጋመሽ ከተማ ነበረ።
የኡሩክ ነገሥታት
፩ ኡሩክ
- ኤንመርካር - የኡሩክ መስራች
- ሉጋልባንዳ - የኤንመርካር ሻለቃ
- ዱሙዚድ፣ አሣ አጥማጁ
- ጊልጋመሽ - የሉጋልባንዳ ልጅ
- ኡር-ኑንጋል - የጊልጋመሽ ልጅ
- ኡዱል-ካላማ፣ ላባዕሹም፣ ኤን-ኑንታራህ-አና፣ መሽ-ሄ፣ መለም-አና፣ ሉጋል-ኪቱን - ስለነዚህ 6 ነገሥታት ምንም አይታወቅም። በዚህ ዘመን ላዕላይነቱ በሱመር ወደ ኡር፣ ከኡርም ወደ አዋን፣ ከአዋንም ወደ ኪሽ፣ ከኪሽም ወደ ሐማዚ እንደ ተዛወረ ይመስላል።
፪ ኡሩክ
- ኤንሻኩሻና - ላዕላይነቱን ወደ ኡሩክ መለሰው። ከርሱ በኋላ ግን ወደ ላጋሽ ተዛወረ።
- ሉጋል-ኪኒሼ-ዱዱ
- አርጋንዴአ
ከዚህ በኋላ፣ ላጋሽ፣ አዳብ፣ ማሪ፣ አክሻክ፣ ኪሽ፣ ኡርና ኡማ ላዕላይነቱን ለመያዝ ይወዳደሩ ነበር።
፫ ኡሩክ
፬ ኡሩክ
፭ ኡሩክ
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |