ጊልጋመሽ
ጊልጋመሽ (ወይም ቢልጋመሽ፥ በቅድመኞቹ ሱመርኛ ጽላቶች) የኡሩክ 4ኛው ንጉሥ ነበረ። በሱመራዊ ነገሥታት ዝርዝር ላይ 126 ዓመታት እንደ ነገሠ ይጠቀሳል። እንዲሁም የጊልጋመሽ ትውፊት የሚባለው ሥነ ጽሑፍ አለ። በዚህ በኩል አባቱ ሉጋልባንዳ ይባላል። ጊልጋመሽም በኡሩክ የነገሰው ከሉጋልባንዳ ተከታይ ከዱሙዚድ፣ አሣ አጥማጁ ቀጥሎ እንደ ነበር ይባላል።
በአንዱ ጽላት የኤንመባራገሲ ልጅ የኪሽ ንጉስ አጋ ከጊልጋመሽ ጋር ሲዋጋው፣ ጊልጋመሽ አሸነፈው። ኤንመባራገሲና አጋ ታሪካዊ የኪሽ ነገሥታት መሆናቸው በስነ ቅርስ ረገድ እርግጠኛ ስለ ሆነ፤ ጊልጋመሽ ደግሞ አፈታሪካዊ ብቻ ሳይቀር ታሪካዊ ንጉስ እንደ ሆነ ይገመታል። ሌላ ሰነድ የቱማል ጽሑፍ እንደሚለን፣ ጊልጋመሽ የኒፑር ቤተ መቅደስ ከኪሽ ያዘ። ይህም ቤተ መቅድስ በሱመር ሙሉ ሥልጣን የሰጠ ሆነ።
ቀዳሚው ዱሙዚድ፣ አሣ አጥማጁ |
የኡሩክ ንጉሥ (ሉጋል) 2375-2350 ዓክልበ. ግድም |
ተከታይ ኡር-ኑንጋል |
ቀዳሚው የኪሽ ንጉሥ አጋ |
የሱመር (ኒፑር) አለቃ 2375-2350 ዓክልበ. ግድም |