ዳው ዴ ጂንግ
ዳው ዴ ጂንግ (ቻይንኛ፦ 道德經 «የምግባር መንገድ ጽሑፍ») በ540 ዓክልበ. ገደማ በቻይናው ፈላስፋ ላው ድዙ የተጻፈ የእምነትና የፍልስፍና ጽሑፍ ነው። ይህ መጽሐፍ የዳዊስም ሃይማኖት መሠረት ሆኗል።
የጽሑፉ መጀመርያ ዓረፍተ ነገሮች በተለይ ዝነኛ ናቸው፦
- 道可道,非恆道;名可名,非恆名。
- በፑቶንግኋ ዘመናዊ ቻይንኛ፦ «ዳው ኬ ዳው ፈይቻንግ ዳው። ሚንግ ኬ ሚንግ ፈይቻንግ ሚንግ።»
- በጥንታዊ ቻይንኛ እንደሚታሰብ፦ «ክሉሕ ኻሕ ሉሕ ፑዊ ገንግ ክሉሕ። መንግ ኻሕ መንግ ፑዊ ገንግ መንግ።»
- ትርጉም፦ «የዘላለሙ መንገድ ሊነገር የሚችል መንገድ አይደለም። የዘላለሙ ስም ሊሰየም የሚችል ስም አይደለም።»
በተረፈ የጽሑፉ ሌላ ታዋቂ ፍሬ ነገር (ምዕራፍ 67) እንዲህ ይላል፦
- «ሦስት ውድ ሀብቶች በውስጤ ምንጊዜም አሉኝ። መጀመርያው ምኅረት፣ ሁለተኛው ቁጠባ፣ ሦስተኛውም የዓለም ቀዳሚ ለመሆን አለመድፈር (ትሕትና)።»
ተመሳሳይ ትምህርት አስቀድሞ ለእስራኤል ነቢይ ሚክያስ (700 ዓክልበ. ግድም) በትንቢተ ሚክያስ 6:8 ተሰጠ፤ «እግዚአብሔርም ከአንተ ዘንድ የሚሻው ምንድር ነው? ፍርድን ታደርግ ዘንድ፣ ምሕረትንም ትወድድ ዘንድ፣ ከአምላክህም ጋር በትሕትና ትሄድ ዘንድ አይደለምን?»።
http://skymon.binoniq.net/2020/03/31 https://archive.org/details/20200331_20200331_1659/mode/2up